መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 10፤2014-የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለዶ/ር እንግዳ አበበ ገላን አፀደቀ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሕክምና ኮሌጅ የዶ/ር እንግዳ አበበን መረጃዎች ከገመገመ በኋላ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ ::ፕሮፌሰር እንግዳ አበበ ገላን የሕክምና ዲግሪያቸውን (MD) ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ፣ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊቲ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቀዶ ህክምና እንዲሁም የሰብ-ስፔሻሊቲ ዲግሪያቸውን በኩላሊት ንቅለ ተከላ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ አግኝተዋል።

እንደሁም የተለያዩ አጫጭር የሞያ ስልጠናዎችን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ተከታትለዋል፡፡ፕሮፌሰር እንግዳ አበበ ገላን በግላቸውና ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር ከ40 በላይ በምርምር የተደገፉ ጥናታዊ ፅሁፎችን በታወቁ ሀገራዊና አለምዓቀፋዊ መፅሄቶች ላይ ለህትመት አብቅተዋል፡፡

ከነዚህም መካከል 15ቱ ተገምግመው የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለማግኘት ከሚጠበቅባቸው 40 የህትመት ነጥብ 62.5 አስመዝግበዋል። በተጨማሪም የተለያዩ ኃላፊነቶችን በመውሰድ በታላቅ ትጋት ለኮሌጁ አገልግሎት የሰጡ ሲሆን በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎቶችና የሙያ ነክ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

በቀዶ ህክምና የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው ፕሮፌሰር እንግዳ አበበ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሕክምና ኮሌጅ በሚገኘው የህክምና ትምህርት ቤት ውስጥ የቀዶ ህክምና ትምህርት ክፍል ሀላፊ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *