መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 14፤2014-የሀሰተኛ ሰነድ መበራከት ስራዬ ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል ፈጥሮብኛል ሲል የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታወቀ

በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከ230 በላይ ሀሰተኛ ሰነዶችን ተገልጋዮች ለመገልገል ይዘዉ መምጣታቸውን የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል፡፡በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ባሉት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ውስጥ በስድስት ወራት ውስጥ ከ230 በላይ ሀሰተኛ ሰነዶች መያዛቸውን የአገልግሎቱ የህግ ጉዳዮች እና ሰነዶች ዝግጅት ዳሬክተር አቶ ተስፋዬ አሰፋ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ከነዚህ ሀሰተኛ ሰነዶች ውስጥ 191 የሚሆኑት ሳይያዙ የቀሩ እና እጃቸው ላይ ያሉ ሀሰተኛ ሰነዶች ሲሆኑ ከ30 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ተይዘው ለህግ መተላለፋቸውን አንስተዋል፡፡191 ከሚሆኑት በሀሰተኛ ሰነድ ለመገልገል የመጡና አምልጠዉ የጠፉ የተገልጋዮችን ፋይል እጅ ከፍንጅ በመያዝ ለተቋሙ ህግ ጉዳየችና ሰነድ ዝግጅት ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡

ወደ አገልግሎቱ ከመጡ ሰነዶች መካከል 121 ሀሰተኛ መታወቂያ 61 ሀሰተኛ ያላገባ ሰነድ፣ አንድ ሀሰተኛ የጋብቻ ማስረጃ አንድ ፤ተመሳስለው የተሰሩ የውክልና ማስረጃ ስድስት እና ሌሎች ማስረጃዎች መሆናቸውን አቶ ተስፋዬ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡አገልግሎቱ ከሚሰጥባቸው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ውስጥ ሀሰተኛ ሰነዶች በብዛት የሚያዙበት በየትኞቹ ናቸው ብሎ ብስራት ሬድዮ ለአቶ ተስፋዬ ላነሰቃዉ ጥያቄ ሀሰተኛ ማስረጃዎች በሁሉም ቅርንጫፎች ቢመጡም ሀሰተኛ ሰነዶችን በቀላሉ የሚለዩ ባለሙያዎች ባሉበት ቅርንጫፎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው እንሚያዝ ተናግረዋል፡፡

በተለይ ስድስት፣ ሰባት እና አስራ አንድ በሚባሉት ቅርንጫፎች በቀን በርካታ ቁጥር ያላቸው ሀሰተኛ ሰነዶች እንደሚያዙ አስረድተዋል፡፡

በትግስት ላቀዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *