👉 ኳታር ይህንን የአለም ዋንጫ ለማዘጋጀት ከ12 ዓመት በፊት አሜሪካን አሸንፋ ስትመረጥ 6 ሚሊዮን ዶላር ለአፍሪካ ሀገራት ፌዴሬሽኖች አከፋፍላለች የሚል መረጃ ቢናፈስም በማስረጃ ማረጋገጥ አልተቻለም።
👉በዶሃ የሚገኘው የማሪዮት ሆቴል የምግብ ቡፌ 100 ሜትር ርዝመት ያለዉ ሲሆን በምግብ ዓይነት የታጨቀ ቡፌ በሚል ይገለፃል።
👉ለውድድሩ 90 በመቶ ትኬት ተሸጦ የተጠናቀቀ ሲሆን የኳታር፣አሜሪካና ሳዑዲ አረቢያ ዜጎች ዋንኛ ገዢዎች ናችው። የአልኮል መጠጥ ለመጠጣት የተፈቀደው በአንድ ፈን ዞን ውስጥ ብቻ ነው።
👉 በኳታር 3 ወንድ ለ1 ሴት የጾታ ምጣኔ ያለ ሲሆን ከፍተኛ የወንዶች ቁጥር ያለባት ሀገር ያደርጋታል፡፡
👉 ኳታር የ 3 ሚሊዮን ሰዎች የመኖሪያ ሀገር ስትሆን ከዓለም ህዝብ 0.04% በመቶኛ ትወክላለች፡፡99 በመቶ የኳታር ነዋሪዎች በከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን ከ90% በላይ የሚሆነው የኳታር ህዝብ በዋና ከተማዋ ዶሃና አካባቢዋ ላይ ይኖራል።
👉 በኳታር ከሚኖረዉ ህዝብ 12% ብቻ የኳታር ዜግነት ያለው ሲሆን የተቀሩት የውጭ ሀገራት ዜጎች ናቸው። ከነዚህ ዉስጥ 60 በመቶ የሚሆኑት ከደቡብ እስያ ሀገራት ከህንድ፣ ፓኪስታንና ባንግላዲ የመጡ ናቸው፡፡
መልካም እድል ኳታር قطر حظا سعيدا
በስምኦን ደረጄ