መደበኛ ያልሆነ

ጥር 17፤2015-ሕንድ እና ፓኪስታን ወደ ኒዉክሌር ጦርነት ተቃርበዉ ነበር ሲሉ ማይክ ፖምፔዮ ተናገሩ

የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በአዲሱ የማስታወሻ መጸሀፋቸዉ ላይ ህንድ እና ፓኪስታን በ2019 ዓመት ለኒዉክሌር ግጭት ተቃርበዉ እንደነበር ተናግረዋል።ይህ ሊሆን የቻለዉ በካሽሚር የሕንድ ወታደሮች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በፓኪስታን ግዛት ውስጥ በሚገኙ ታጣቂዎች ላይ ህንድ የአየር ላይ ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ ነዉ፡፡

በወቅቱ ፓኪስታን በአጸፋዉ ሁለት የህንድ የጦር ጄቶች መትታ የጣለች ሲሆን አንድ ተዋጊ አብራሪን መያዙን ማስታወቋ ይታወሳል፡፡ህንድ እና ፓኪስታን ሁሉንም የካሽሚር ግዛት ይገባኛል በሚል የሚወዛገቡ ሲሆን ሁለቱም ሀገራት ግን የተወሰነውን ክፍል ብቻ ተቆጣጥረዋል፡፡

ህንድ በካሽሚር ሸለቆ ውስጥ ያሉትን ተገንጣይ ታጣቂዎችን ትደግፋለች ስትል ፓኪስታን ስትወነጅል ኖራለች፡፡ ፓኪስታን በበኩሏ ውንጀለዋ አስተባብላለች። የኒውክሌር የጦር መሳሪያን የታጠቁ ጎረቤት ሀገራቱ ከብሪታንያ ነፃ ከወጡበት ከ1947 አንስቶ ሦስት ጦርነቶችን አካሂደዋል። ከአንዱ በስተቀር ጦርነት በስተቀሩ የሁለቱ ዉጊያ በካሽሚር ላይ ነበር።

የህንድ-ፓኪስታን ፉክክር በየካቲት 2019 ምን ያህል ወደ ኒውክሌር ግጭት ሊሸጋገር እንደሚችል አለም በትክክል የሚያውቅ አይመስለኝም ነበር ሲሉ ፖምፒዮ ገልጸዋል፡፡”እውነታው ግን በጣም ቅርብ እንደነበር አውቃለሁ” ሲሉ ጽፈዋል።

ፖምፔዮ “ሌሊቱን ፈጽሞ አልረሳውም” በሃኖይ “ከሰሜን ኮሪያውያን ጋር በኒውክሌር ጦር መሳሪያ ላይ አሜሪካ ስትደራደር” በተካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ላይ “ህንድ እና ፓኪስታን በሰሜን አዋሳኝ የድንበር አካባቢ ለአስርት አመታት ከዘለቀው ውዝግብ ጋር በተያያዘ እርስ በርስ ዛቻ ዉስጥ ገብተዉ”ነበር ሲሉ በማስታወሻቸዉ ላይ አስፍረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *