መደበኛ ያልሆነ

ጥር 17፤2015-ኢትዮጲያ የተፈጨ የአህያ ስጋን ወደ ቻይና መላክ ልትጀምር ነዉ

ኢትዮጲያ የተፈጨ የአህያ ስጋን ወደ ውጪ ሀገራት ለመላክ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀች እንደምትገኝ በአሰላ ከተማ የሚገኘው ሮንግ ቻንግ የተባለው የአህያ ቄራ ድርጅት አስታዉቋል።የድርጅቱ አስተባባሪ አቶ ቺቺ አማን ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ የአህያ ስጋን ምንም እሴት ሳትጨምርበት ወደ ምስራቅ እስያ ሀገራት ስትልክ ብትቆይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን በአለም አቀፍ ገበያ ላይ የምርቱ ተፈላጊነቱ እየቀነሰ መጥቷል።

በዚህም የተነሳ በ2015 በጀት አመት ስድስት ወራት ውስጥ የአህያ ስጋ ወደ ውጪ ሀገራት አለመላኩን ጠቁመዋል፡፡ኢትዮጵያም ባለፉት ስድስት ወራት ከአህያ ስጋ የወጪ ንግድ ገቢ አለማግኘቷን ገልጸዋል፡፡ይህንን ችግር ከመፍታት አኳያ የተፈጨ የአህያ ስጋን ወደ ቻይና ሆንግኮንግ ለመላክና ኢትዮጵያም ከዘርፉ ተጠቃሚ እንድትሆን ለማድረግ ዝግጅቶች መደረጋቸውን አቶ ቺቺ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ይህንን ስራ ለማከናወን የማሽን ተከላና የሰው ሀይል የማሟላት ዝግጅቶች እየተከናወነ ይገኛል፡፡በዚህ መልኩ የአህያ ስጋን ለውጪ ገበያ እንዲቀርብ ማድረጉ ከዚህ በፊት ከአንድ ኪሎ የአህያ ስጋ ሽያጭ ይገኝ የነበረውን የአንድ የአሜሪካን ዶላር ገቢን እስከ አራት የአሜሪካን ዶላር ከፍ እንደሚያደርገዉ ታምኖበታል፡፡

በቅድስት ደጀኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *