መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 16፤2015-የሴኔጋል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በማሳጅ ቤት ውስጥ የምትሰራ ሴት ላይ የአስገድዶ መድፈር የወንጀል ክስ መታየት ጀመረ

???? የፖለቲከኛው ደጋፊዎች እንዳይያዙ በሚል መንገድ ዘግተዋል

የሴኔጋል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የቀረበባቸው ክስ እንደቀጠለ ቢሆንም ኦስማን ሶንኮ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ አልቻሉም።የጸጥታ ሃይሎች በዋና ከተማዋ ዳካር የተቃዋሚው ፓርቲ ደጋፊዎች የፀጥታ ችግር እንዳይፈጥሩ በመፍራት የዳካር ከተማ ጎዳናዎች በቁጥጥር ስር አድርገዋል።

የተቃዋሚ ፓርቲው መሪ ሶንኮ በወጣቶች ዘንድ እጅግ በጣም ተወዳጅ ናቸው። የ48 አመቱ ፖለቲከኛ ባሳለፍነው ሳምንት የተጀመረው የፍርድ ሂደት ፖለቲካዊ አላማ ያለው እና በሚቀጥለው አመት ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እጩ ሆነው እንዳይቀርቡ ሆን ተብሎ የተመሰተተ ክስ ነው ሲሉ የወንጀል ክሱን አጣጥለዋል።

በማሳጅ ቤት ውስጥ የምትሰራ ሴት ላይ ጾታዊ ጥቃት ማድረሳቸውንና በእሷ ላይ የግድያ ዛቻ ሰንዝረዋል መባሉን ክደዋል። የቀድሞ የግብር ተቆጣጣሪና በደቡባዊቷ ዚጊንኮር ከተማ ከንቲባ የነበሩት ሶንኮ ድርጊቱን በከንቲባነት ዘመናቸው እንደፈፀሙት ይታመናል ሲል AFP የዜና ወኪል ዘግቧል።

ተቃዋሚዎች ሶንኮ ሊያዙ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማስቀረት ወደ ቤታቸው የሚወስደውን መንገድ በመዝጋት ላይ ይገኛሉ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *