መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 17፤2015-በአዲስ አበባ ቡልቡላ ድልድይ ላይ አንድ ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት አለፈ

???? ሟች በተገጨበት ወቅት ከድልድዩ ወደ ወንዝ ውስጥ ገብቷል

በአዲስ አበባ ከተማ ግንቦት 16 ምሽት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታዉ ቡልቡላ አካባቢ በሚገኝ ድልድይ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት አደጋዉ ያደረሰዉ ተሸከርካሪ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 47681 የሆነ የቤት አዉቶሞቢል ሲሆን አደጋዉ የደረሰዉ በእግረኛ መንገድ ላይ በነበሩ መንገደኞች ላይ ነው።ጉዳት የደረሰባቸዉ ሁለት ተጎጂዎች  ወዲያዉኑ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡በአደጋዉ የ35 ዓመት ወጣት በተሽከርካሪዉ ተገጭቶ  20 ሜትር ርቀት ወዳለዉ ወንዝ ዉስጥ በመግባት ህይወቱ አልፏል፡፡

ህይወቱ ያለፈዉን ሰዉ አስከሬን ከእሮብ ምሽት ጀምሮ ፍለጋ ሲያካሂዱ የነበሩት የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመ ራር ኮሚሽን ጠላቂ ዋናተኞች አስከሬኑን 20 ሜትር ርቀት ካለዉ ገደልና ወንዝ ዉስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ሀሙስ እለት አግኝተዋል፡፡አስከሬኑን በማዉጣት ለፖሊስ ማስረከባቸውን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በትግስት ላቀዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *