መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 17፤2015-ዘመን ባንክ በሚቀጥለዉ አመት ካፒታሉን ወደ 15 ቢሊዮን ብር ያሳድጋል ተባለ

???????? ባንኩ ግምታዊ ወጪዉ 1.5 ቢሊዮን ብር ፈሰሰ ያደረገበትን ህንጻ ከነገ በስቲያ ያስመርቃል

ዘመን ባንክ ከሚቀጥለዉ አመት ጀምሮ ካፒታሉን ወደ 15 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ከዉሳኔ መድረሱን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ዘነበ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

በ 87.2 ሚሊዮን ብር ካፒታል ከተመረተ 15 አመታት ገደማ ያስቆጠረዉ ባንኩ ፤ 40 ቢሊዮን ብር ሀብት ላይ መድረሱን አቶ ደረጀ አንስተዋል። ባንኩ በከፍተኛ እድገት ላይ ይገኛል ያሉት ስራ አስፈፃሚዉ ፤ ባመፉት አምስት አመታት በአማካይ 40 በመቶ እድገት እንዳስመዘገበ ተናግረዋል። በተጨማሪም በዘንድሮው አመት ከታክስ በፊት 3 ቢሊዮን ብር ትርፍ እንጠብቃለን ብለዋል።

የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኤርሚያስ እሸቱ እንደገለጹት ፤ ባንኩ በመጪዉ ቅዳሜ ግምታዊ ወጪዉ 1.5 ቢሊዮን ብር ገደማ ፈሰስ ያደረገበትን ባለ 36 ወለለ ህንጻ ያስመርቃል ብለዋል።

ህንጻዉ ለሰራተኞቹ የህጻናት ማቆያ ፣ የስፖርት ማዘዉተሪያ ጂምናዚየም ፣ መዝናኛ ክበቦች እና የስራ ማስኬጃ ቢሮ ያለዉ ነዉ። ከ 200 በላይ መኪናዎች ማቆም ይችላል በተባለለት ህንጻ ከወለል በታች አስተማማኝ የገንዘብ እና  የከበሩ ማድናት ማስቀመጫ እንዲሁም የሰነድ ክፍል እንደሚኖረዉ ተገልጿል። በተጨማሪም አስተማማኝ የተባለ የመረጃ ቋት እንዳለዉም ተነግሯል። ባንኩ ከዚህ ቀደም ለኪራይ ህንጻ በየአመቱ 40 ሚሊዮን ብር ወጪ ያደርግ እንደነበርና ይህንን እንደሚያስቀርለትም አቶ ደረጀ ገልጸዋል።

ባንኩ በአሁን ወቅት 35 ቢሊዮን ብር የቁጠባ ገንዘብ መጠን ላይ መድረሱን  እና 35 ቢሊዮን ብር የብድር አቅርቦት መስጠቱን ዋና ስራ አስፈጻሚዉ አቶ ደረጀ አንስተዋል። በተያዘዉ አመትም ከታክስ በፊት 3 ቢሊዮን ብር ትርፍ እንደሚጠበቅ አቶ ደረጀ ጨምረዉ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *