መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 17፤2015-የቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ ፓርክ ሰራተኛ በስራ ላይ እያለ በኤሌክትሪክ ተይዞ ህይወቱ አለፈ

በዛሬው እለት ግንቦት 17 ቀን ከረፋዱ 5:49 ደቂቃ ላይ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5  የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሰራተኛ በኤሌክትሪክ ተይዞ ህይወቱ ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ሟቹ ዕድሜዉ 35 ዓመት የተገመተ ሲሆን በኢንዱስትሪ ፖርኩ ውስጥ የኤሌክትሪክ ባለሞያ ነበር። አደጋዉ ያጋጠመዉ በሚሰራበት ፋብሪካ ቤዝመንት ውስጥ በስራ ላይ እንዳለ ነበር።

የወጣቱን አስከሬን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከቤዝመንት ዉስጥ አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *