በሸገር ከተማ በዛሬው እለት ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም አንፎ አደባባይ አካባቢ ተቆፍሮ ክፍቱን በተተወ ጉድጓድ ዉስጥ እድሜዉ 19 ዓመት የሆነ ወጣቱ ህይወቱ አልፎ መገኘቱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ወጣቱ ህይወቱ ያለፈዉ ምንም ዓይነት የውሃ ዋና ችሎታ ሳይኖረዉ ለመዋኘት በመግባቱ የተነሳ እንደሆነ ገልፀዋል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጠላቂ ዋናተኞች የወጣቱን አስከሬን አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።
በአዲስ አበባና አካባቢዉ ክፍቱን በተተዉ ጉድጓዶች ዉስጥ ውሃ ዋና ለመዋኘት በሚል በርካታ ህጻናትና ታዳጊዎች ህይወታቸዉን እያጡ በመሆኑ ክፍቱን የተተዉ ጉድጓዶችን የሚመለከታቸዉ አካላት እንዲደፈኑ እንዲሁም ታዳጊዎችና ወጣቶች በእነዚህ ስፍራ ያላቸዉን እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ ኮሚሽኑ አሳስቧል።
በትግስት ላቀው