መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 18፤2015-በትግራይ ክልል በነበረዉ ጦርነት ከ2 ሺህ 1 መቶ በላይ መምህራን መገደላቸዉን የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ

የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በትግራይ ክልል በተከሰተው ጦርነት የተነሳ የተከሰተውን ቀውስ አስመልክቶ ባካሄደው ቁጥጥር ላይ ያገኛቸውን ግኝቶች በማስመልከት ይፋ አድርጓል፡፡

በተቋሙ የአስተዳደር በደል መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዳነ በላይ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በክልሉ በተከሰተው ጦርነት ሳቢያ 2ሺህ 1መቶ 46 የሚሆኑ መምህራን ህይወታቸዉ አልፏል፡፡አያይዘው የ 1 ሺህ 7 መቶ ተማሪዎች በግጭቱ የተነሳ ህይወታቸዉ ማለፏን ተቋሙ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ባገኘው መረጃ ማወቅ እንደቻለ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ትምህርት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ በጦርነቱ ወቅት  ከተቀበሩ ፈንጂዎችና  ተተኳሸ መሳሪያዎች ባለመጽዳታቸው የተነሳ ቁጥራቸዉ በዉል ያልተገለጹ ሰዎች ለአካል ጉዳት መዳረጋቸው በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡በጦርነቱ ምክንያት በክልሉ በትምህርት ሴክተር ላይ በደረሰ የጉዳት መጠን የገንዘብ ተመንን በተመለከተ ተቋሙ እያካሄደ ያለው ጥናት የቁጥጥር ስራው እስከተካሄደበት ቀን ድረስ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ መረጃውን ማግኘት አለመቻሉን አቶ አዳነ በላይ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በቅድስትደጀኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *