መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 18፤2015-ቻይና የኬንያ የመንግስት ተቋማት ላይ ጠለፋ ፈጽማለች መባሏን አስተባበለች

በኬንያ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ የሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገባን አስተባብሏል፡፡ የቻይና ሰርጎ ገብ የድህረ ገጽ መንታፊዎች በዋና ከተማዋ ናይሮቢ የሚገኙ የፕሬዚዳንቱን ጽህፈት ቤት ጨምሮ ቁልፍ በሆኑ የመንግስት ተቋማት ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል መባሉን የቻይና መንግስት አስተባብሏል፡፡

ጠለፋዉ የተፈጸመዉ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር የሆነችዉ ኬንያ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ብድርን ከመክፈል ጋር በተያያዘ ናይሮቢን ለመገምገም ያለመ ነዉ ተብሏል፡፡የሳይበር ጥቃቱ እ.ኤ.አ በ2019 የጀመረ ሲሆን የኬንያ የዕዳ ጫና መታየቱን ተከትሎ ናይሮቢ ከቻይና መበደር በማቆሟ የተነሳ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።የቻይና ኤምባሲ ግን ዘገባዉን ተሞርክዞ በሰጠው መግለጫ “ከእውነት የራቀ እና ከንቱ ክስ” ሲል አጣጥሎታል።

“የሰርጎ  ገቦች ጥቃት የሁሉም ሀገራት የተለመደ ስጋት ሲሆን ቻይናም የሳይበር ጥቃት ሰለባ ነች” ሲል ኤምባሲዉ አክሏል።ያለ በቂ ማስረጃ አንድን መንግስት ለሳይበር ጥቃት ተጠያቂ ማድረግ እጅግ አሳሳቢ የፖለቲካ ጉዳይ ነው ሲል ኤምባሲው ተናግሯል።

በኬንያ እና በቻይና መካከል ያለው ግንኙነት በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ ነው በማለት”ቻይና እና ኬንያ ጥሩ ጓደኞች፣ ጥሩ አጋሮች እንዲሁም ጥሩ ወንድማማቾች ናቸው” ሲል የኤምባሲው ቃል አቀባይ አስታዉቋል።ኬንያ ከቻይና የምትወስደውን ብድር ማቋረጧ መናገሯ አይዘነጋም፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *