
???? በኪሎ ከ 70 እስከ 80 ብር እየተሸጠ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ የቀይ ሽንኩርት ዋጋ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ሸማቾች ቅሬታቸዉን ለብስራት ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡ሽንኩርት በኪሎ ከ70 እስከ 80 ብር እየተሸጠ መሆኑን የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ በተለይ በአንድ ሳምንት ውስጥ የ40 ብር ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል።
በአሁኑ ሰአት ገቢያቸው እና ኑሮው እየተመጣጠነ አለመሆኑ እና የሚፈልጉትን ሸምተው መኖር አለመቻላቸው ኑሮአቸውን እንዳከበደውም ነዋሪዎች አክለዋል ።ብስራት ሬዲዮ በተለያዩ የገበያ ስፍራዎች ተዘዋውሮ ለማየት እንደሞከረው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ከመኖሩ ባሻገር አቅርቦቱ ከእለት እለት እየቀነሰ መሆኑን ሃሳባቸውን ለጣቢያችን ከገለጹ ነጋዴዎች ለመገንዘብ ችለናል ።
ብስራት ሬዲዮ ጉዳዩን በተመለከተ ምክንያቱ ከምን የመጣ ነዉ የሚለዉን ለማጣራት የከተማዉ ንግድ ቢሮ የሚመለከታቸውን አካለት ለማናገር በተደጋጋሚ የስልጥ ጥሪ ቢያደርግም ምላሽ ማግኘት አልቻለም፡፡እንዲሁም በአካል ተገኝታችሁ ጠይቁ የተባለ በመሆኑ በቀጣይ በሌላ ዘገባ ምላሻቸዉን አካተን ይዘን እንመለሳለን፡፡
በሳምራዊት ስዩም