መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 7፤2015-በጃፓን ላይ ከተጣለዉ የአቶሚክ ቦምብ በሶስት እጥፍ የበለጠ የኒዉክሌር ጦር በቤላሩስ ሩሲያ ልታከማች ነዉ

???? የቤላሩስ ፕሬዝዳንት “መሳሪያዉን ለመጠቀም ዉሳኔ እንዳልሰጥ እግዚያብሄር ይጠብቀኝ ” ብለዋል

የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በሰጡት መግለጫ ሀገራቸው በሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ከተጣሉ የአቶሚክ ቦምቦች “በሶስት እጥፍ የሚበልጡ” የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን ከሩሲያ እየተቀበለች እንደሆነ ጠቁመዋል። ቤላሩስ ሊደርስባት የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል ወደ የጦር መሳሪያዉ አስፈላጊ እንደሆነ አስታዉቃለች።

ከቀናት በፊት ሩሲያ እንዳስታወቀችው ከሆነ ከሀምሌ ወር አንስቶ ታክቲካል የኒውክሌር ጦር መሳሪያን በቤላሩስ ምድር እንደምታሰማራ ገልፃለች። ይህን ለምዕራቡ ዓለም እንደ ማስጠንቀቂያ ተደርጎ ተወስዷል። ሉካሼንኮ እንዳስታወቁት ሚንስክ የጦር መሳሪያዎቹን ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል። “ሁሉም ነገር ዝግጁ ነው። የጠየቅነውን በጥቂት ቀናት ውስጥ ትንሽም ቢሆን የምናገኝ ይመስለኛል” ሲሉ ተናግረዋል።

ሉካሼንኮ በምዕራባውያኑ ሀገራት አነሳሽነት ጥቃት የሚሰነዘርብን ከሆነ ምላሽ ለመስጠት መሳሪያውን ከመጠቀም ወደኋላ እንደማይሉ አስጠንቅቋል። “ለምን የኒውክሌር የጦር መሳሪያእን እንደምንፈልግ ልንገራችሁ አንድም የውጪ ወታደር በቤላሩስ ምድር ላይ እግሩን ካሰረፈ እንጠቀምበታለን” ሲሉ ተናግረዋል።

“እግዚያብሄር እነዚህን መሳሪያዎች ለመጠቀም ውሳኔ እንዳልሰጥ ይጠብቀኝ። ነገር ግን በኛ ላይ ጥቃት ሲሰነዘር ማመንታት እንደማይኖር እወቁት ሲሉም አክለዋል። ከሶቪየት ኅብረት መፍረራረስ በኋላ ሩሲያ የጦር መሳሪያዎችን ስታንቀሳቅ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *