መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 7፤2015-ዶናልድ በኢትዮጲያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 250ሺ የሚሆኑ ሰዎች ደም መለገሳቸዉ ተነገረ

???? የደም ለጋሾች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ በትላንትናዉ እለት ተከብሯል

የዓለም ደም ለጋሾች ቀን “ደም ይለግሱ፤ ህይወትን ያጋሩ፤ ዘውትር ያጋሩ” በሚል መሪ ሃሳብ በዛሬዊ እለ በአሶሳ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል፡፡ቀኑ በኢትዮጲያ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾች ለለገሱት ክቡር ደም እንዲሁም ለታደጉት ህይወት ለማክበርና ለማመስገን ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በኢትዮጽያ በየሶስት ወሩ በቋሚነት ደም የሚለግሱ ሰዎች ሲኖሩ ለእነርሱና ለመላዉ በጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾች በማርሽ ባንድ በታጀበ የእግር ጉዞ ምስጋና ቀርቦላቸዋል፡፡በ2015 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተሰራዉ ሪፖርትም 250 ሺ ገደማ የሚጠጉ የማህበረሰብ ክፍሎች ደም የለገሱ ሲሆን በቂ ባይሆንም መልካም መነቃቃት እየታየበት መሆኑም በኢትዮጵያ ደምና ህብረህዋስ ባንክ አገልጥሎት የደም ለጋሾች ክፍል አስተባባሪ ሲስተር ሀና ለገሰ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በኢትዮጲያ ባሉ የተለያዩ ግጭቶች፣በወሊድ እንዲሁም የካንሰር ታማማሚዎች ማዕከላት በስፋት እየተገነቡ መሆኑን ተከትሎ የደም ፍላጎቱ ሲጨምር ማህበረሰቡን ለማነቃቃትና ግንዛቤ ለማስጨበትም በየአደባባዩ በስፋት እየተሰራበት እንደሚገኝ አክለዋል፡ ሁለንተናዊ ደህንነቱ የተጠበቀ ደም ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት ትኩረት በመስጠት እየሰራ ይገኛል፡፡

በአብርሃም ፍቅሬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *