መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 7፤2015-ዶናልድ ትራምፕ ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ተናገሩ

ዶናልድ ትራምፕ በማያሚ ፍሎሪዳ በሚገኘው የፌደራል ፍርድ ቤት ሚስጥራዊነት ያላቸውን ሰነዶች አላግባብ በመያዝ በተከሰሱበት ታሪካዊ ክስ ጥፋተኛ አይደለሁም ሲሉ ተናግረዋል።ትራምፕ በፌዴራል የወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ናቸው።

እጃቸውን አጣምረው፣ ጥቁር ልብስ በቀይ ክራባት አድርገው በዓመቱ ለሁለተኛ ጊዜ የፍርድ ቤት ውሎ የቀረቡት ትራምፕ ፊታቸውን ሳይፈቱ ከችሎቱ ወጥተዋል። ከችሎቱ  በኋላ በቤድሚንስተር ኒው ጀርሲ ወደሚገኘው የጎልፍ ክለብ በመጓዝ  ለደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገዋል። ለ2024 የሪፐብሊካን ፕሬዚዳንታዊ እጩነት ግንባር ቀደም የሆኑት ትራምፕ ሚስጥራዊ ሰነዶችን ለመያዝ “መብት” እንዳላቸው ለተሰበሰበው ህዝብ ተናግረው ነገር ግን ሁሉንም ሂደት የማለፍ እድል እንዳልነበራቸው ገልፀዋል።
ህጉን ተከትዬ የመጣሁ ሰው ነኝ በማለት በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና በቀድሞ ተቀናቃኛቸው ሂላሪ ክሊንተን ላይ  ቅሬታዎችን ዘርዝረዋል። ከማያሚ ከመነሳቱ በፊት ቀደም ብሎ ትራምፕ የግላቸው ንብረት በሆነው ማህበራዊ ሚዲያ Truth Social ላይ “ለሀገራችን እንደዚህ ባለ አሳዛኝ ቀን እንዲህ አይነት ሞቅ ያለ አቀባበል ስላደረጋቹልን” ከተማዋን አመስግናለው ሲሉ አጋርተዋል።

በሚያሚ መሃል ከተማ በሚገኘው የፌዴራል ፍርድ ቤት 13ኛ ፎቅ ውስጥ ትራምፕ የቀረበባቸውን 37 የክስ መዝገቦች ጥፋተኛ አይደሉም  ሲሉ ጠበቃቸው ተከራክረዋል ። ጠበቃው ቶድ ብላንች “በእርግጠኝነት ጥፋተኛ አይደለንም ብለን ተከራክረናል” ሲሉ ለዳኛው ተናግረዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *