መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 8፤2015-በባምባሲ ወረዳ ህፃን ልጇን መፀዳጃ ቤት ጥላ ልትሰወር የሞከረች እናት በቁጥጥር ስር ዋለች

በአሶሳ ዞን በባምባሲ ወረዳ በዋምባ ቀበሌ ሰኔ 6 ቀን 2015 ዓ.ም የ18 ዓመቷ ወጣት ከወለደች በኋላ ልጇን መፀዳጃ ቤት ጥላ ልታመጥ ስትል በቁጥጥር ስር እንደዋለች ተነግሯል ።

ወጣቷ በቀበሌው ፑል ማጫወት ተቀጥራ የምትሰራ ሲሆን ሰኔ 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ወልዳ መፀዳጃ ቤት መክተቷን የባምባሲ ወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት የሆኑት ምክትል ኮማንደር ጌታቸው ተረፈ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።

ወጣቷ ዘሀራ አበበ የምትባል ሲሆን ህፃን ወደ ተጣለበት መፀዳጃ ቤት የገባ ሰው የህፃን ድምፅ መስማቱ ተከትሎ ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ አማካኝነት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ወንጀል ፈፃሚዋ በቁጥጥር ስር እንደዋለች ተገልጿል ።

የተጣለው ህፃን ወንድ መሆኑንና በአካባቢው በሚገኝ የህክምና ተቋም የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ ከተደረገለት በኋላ ለተሻለ ህክምና ወደ አሶሳ ሆስፒታል እንደተላከ ተነግሯል ።

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *