መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 9፤2015-በጥቁር ገበያ ዶላር ምንዛሪ ለማድረግ በተገናኙ ግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ፀብ መነሻነት በቁጥጥር ስር ዋሉ

ተጠርጣሪዎች አብርሀም ተስፋገብር እና እስክንድር ፈለቀ የተባሉ ሰኔ 3 ቀን 2015 ዓ/ም በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ቱሪስት ሆቴል አካባቢ ዶላር በጥቁር ገበያ ምንዛሬ ሲያደርጉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በዜግነት ካናዳዊ የሆነ አብርሃም ተስፋ ገብር የያዘውን 6 ሺ ዶላር ከአቶ እስክንድር ፈለቀ ጋር በጥቁር ገበያ ለመለዋወጥ ተገናኝተው በምንዛሬው ላይ መግባባት ላይ ባለመድረሳቸው ወደ ጸብ እንዳመሩ ፖሊስ ገልጿል፡፡

የተፈጠረውን ያለመግባባት ለመፍታት የተገኙ የፖሊስ አባላትም ጉዳዩ የወንጀል ድርጊት በመሆኑ ሁለቱንም ተጠርጣሪዎች ከያዙት 6 ሺህ ዶላርና 137200 የኢትዮጵያ ብር ጋር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርገዋል።

ምንጭ ፡-አዲስ አበባ ፖሊስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *