መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 12፤2015-በሱዳን የሚገኘው የቱኒዚያ አምባሳደር መኖሪያ ቤት ተዘረፈ

በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የታጠቁ ኃይሎች የቱኒዚያን አምባሳደር መኖሪያ ቤት ዘርፈዋል ሲል የቱኒዚያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠዉ መግለጫ “ጥቃቱ በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ የቪየና ስምምነትን የጣሰ እና የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች ዋና መሥሪያ ቤት ያለመንካት መመሪያ መጣስ ነው” ሲል ጠርቶታል።

ሚኒስቴሩ በሱዳን በሚያዝያ ወር የጀመረው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ ባቀረበበት ወቅት ድርጊቱን የፈጸሙ ወንጀለኞች “በክትትል ሂደት በህግ እንዲጠየቁ” ጠይቋል።ጦርነቱ ከጀመረበት ሚያዝያ ወር አንስቶ በካርቱም የሚገኙ በርካታ ኤምባሲዎች ተዘርፈዋል ከነዚህም መካከል የኳታር፣ኩዌት፣ሊቢያ፣ዮርዳኖስና ኦማን ይገኙበታል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *