መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 13፤2015-የጣሪያ እና ግድግዳ ግብርን ምክንያት በማድረግ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ

የከተማ አስተዳደሩ ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በተደረገ ክትትል ደርሰንበታል ብሏል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ውይይት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር የማይቻል መሆኑን መወሰኑን ይታወሳል::

በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በወሰነው ውሳኔ መሰረት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት አይቻልም ማለቱን ከከተማ አስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *