መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 13፤2015-ዩክሬን ትልቁን ቡጢ ገና ሩሲያ ላይ እንዳላሳረፈች አስታወቀች

የዩክሬን ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ሃና ማሊያር ኪዬቭ በሩሲያ ኃይሎች ላይ እየወሰደች ያለው የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ “ትልቁን ምት” ገና ሩሲያ ላይ አለማሳረፏን ተናግረዋል።ነገር ግን ሩሲያ የዩክሬን የመልሶ ማጥቃት ለማደናቀፍ እና ወደፊት እንዳትሄድ ለመከላከል የምትችለውን ሁሉ ወደ ጦርነቱ እየወረወረች መሆኑ አምነዋል።

ዩክሬን በሩሲያ ጦር ተወረረብኝ ያለችውን መሬት ለማስመለስ ከሁለት ሳምንታት በፊት ብዙ ሲወራለትና ሲነገርለት የነበረው የመልሶ ማጥቃት የመጀመሪያ ምዕራፍ ዘመቻ መጀመሯ ይታወሳል። ነገር ግን በዩክሬን ሃይሎች እየተወሰደ ያለው የመልሶ ማጥቃት ሂደት አዝጋሚ መሻሻል የታየበት ሲሆን ሩሲያ በጠንካራ መንገድ ራሷን እየተከላከች መሆኑን በሞስኮ ያሉ ባለስልጣናት የዩክሬን ጥቃት እንዳልተሳካ ጨምረው ገልፀዋል ።

በአጠቃላይ በዘመቻው ላይ ጥብቅ ዝምታን የመረጠው የዩክሬን ጦር አነስተኛ ድሎች እንደተመዘገቡ እና እስካሁን ስምንት መንደሮች ከ113 ካሬ ኪሎ ሜትር ከሚያህል ክልል ጋር ከሩሲያ መዳፍ ነፃ መሆናቸዉን ሰኞ እለት አስታውቋል። ማሊየርበሰጡት መግለጫ በሩሲያ ላይ የምናሳርፈው “ትልቁ ቡጡ ገና ሊመጣ ነው” ሲሉ በቴሌግራም ላይ አጋርተዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *