መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 14፤2015-በናይጄሪያ ካኖ ግዛት በስልክ ስርቆት የተነሳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ

በሰሜናዊ ናይጄሪያ የካኖ ግዛት ባለስልጣናት በካኖ ከተማ በስልክ ዝርፊያ እና ሌሎች የወንጀል ድርጊቶች መበራከታቻውን ተከትሎ ሰኞ እለት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ጉባኤው የከተማዋን ሰላም አደጋ ላይ የሚጥሉ ወንጀሎች የስልክ ዝርፊያ፣ የሱቅ ዝርፊያ፣ የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀም እና ሌሎች ወንጀሎች መበራከታቸው እንዳሳሰበው ገልጿል።

በምክር ቤቱ አብላጫ ድምፅ ባገኘው የውሳኔ ሃሳብ ላይ የጉባኤው አባላት ጉዳዩ ከመባባሱ በፊት አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ ተስማምተዋል። የክልሉ መንግስት ወንጀሉን የፈፀሙ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ውለው ለፍርድ እንዲቀርቡ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ምክር ቤቱ አሳስቧል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *