መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 14፤2015-ቡዳ ሆነህ በልተህኛል በማለት ሰው የገደለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በዳውሮ ዞን ገሳ ከተማ አስተዳደር ከአጉል እምነት በመነሳት ቡዳ ሆነህ በልህተኛል በማለት የግድያ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ተከሳሽ የሆነው ግለሰብ ማርቆስ ምትኩ የሚባል ሲሆን ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 6 ሰዓት የግል ተበዳይ መጠጥ ጠጥቶ ወደውጭ ሲወጣ የተከሳሽን እግር በመርገጡ በአጉል እምነት በመነሳት ቡዳ ሆነህ በልተህኛል ምራቅ ትፋብኝ በሚል መንገድ በመጠበቅ በድንጋይ ደብድቦ ህይወቱን እንዲያልፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

ፖሊስ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር በማዋል ባደረገው ምርመራ የግል ተበዳይ መንገድ በመጠበቅ የግል ተበዳይ ወደ ቤቱ ሲሄድ  በድንጋይ ደጋግሞ በመደብደብ ህይወቱ እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ መሬት ለመሬት  ሲጉትተው የአካባቢው ሰዎች በመድረሳቸው ጥሎ መሸሹን ተገልጿል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ተጠርጣሪውን በመያዝ ለፖሊስ ያስረከቡ ሲሆን ፖሊስ ግለሰቡ ላይ ባደረገው ምርመራ ሰውን በመግደል ወንጀል ክስ መስርቶበት ለፍርድ ቤት ያቀርበዋል።የዳውሮ  ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ ማርቆስ ምትኩ  በ20 አመትፕ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *