መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 15፤2015-በምዕራብ አርሲ ዞን ከበቆሎ እና ማሽላ ጋር የተዘራ አደንዛዣ እፅ እንዲወገድ ተደረገ

በምዕራብ አርሲ ዞን ባለፉት 11 ወራት የአደንዛዥ እፅ ንግድ ዝውውርን ለማስወገድ በተደረገ የቁጥጥር ስራ 334 ኩንታል ሀሺሽ በቁጥጥር ስር መዋሉን የምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል እና የአካባቢ ሰላም ማስከበር ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር አቡበከር አማን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በዞኑ ካሉ 13 ወረዳዎች በአራቱ ወረዳዎች በከፍተኛ መጠን ከበቆሎ እና ማሽላ ዘር ጋራ በመቀላቀል የአደንዣዥ እፅ እንደሚመረት ተገልጿል።በተጨማሪም ባለፉት 11 ወራት በተደረገ ቁጥጥር እና ክትትል 10 ሄክታር መሬት ላይ የተዘራ አደንዛዥ እጽ በማሳ ላይ እንዳለ እንዲወገድ ተደርጓል።

የአደንዛዥ እጽ ዝውውር ላይ እጃቸው አለበት የተባሉ 22 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው 19ኙ ከ ሁለት እስከ 7 ዓመት እስራት እና በገንዘብ መቀጮ ተቀጥተዋል።የአደንዛዥ እጽ ንግድ እና ዝውውር ውስጥ የተሰማሩ ነጋዴዎች እና ደላሎች አርሶ አደሩን በገንዘብ በመደለል ከሰብሎች ጋር አደባልቀው እንዲዘሩ እያደረጉ መሆኑን እና ይህም ከፍተኛ ችግር በመፍጠሩ የቁጥጥር ስራዉ እንዲጠናከር ማድረጉን ኮማንደር አቡበከር አማን ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *