መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 15፤2015-በኬንያ በፈጣን ባቡር ውስጥ የተወለደ ህፃን ኬንያውያንን አስደስቷል

በኬንያ ርዕሰ መዲና ናይሮቢ እና በሞምባሳ የባህር ዳርቻ ከተማ መካከል ባለዉ የፈጣን ባቡር የተሳፈረችዉ እናት በሰላም ልጇን ተገላግላለች፡፡የኬንያ ምድር ባቡር በማህበራዊ ሚዲያ ታሪኩን ካካፈለ በኋላ ኬንያውያን በዚህ ዜና ተደስተዋል ሲል አጋርቷል።

የብሔራዊ የባቡር መሥሪያ ቤቱም ሰራተኞች መካከል አንዷ አዲስ የተወለደውን ህጻንና ከእናትየው ጋር አብረው የሚያሳዩ ፎቶግራፎች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛል፡፡እንደ እድል ሆኖ አንድ ዶክተር እና ነርስ በባቡሩ ውስጥ የነበሩ ሲሆን በወሊድ ጊዜ እገዛ ማድረጋቸዉ ተሰምቷል፡፡

“በኬንያታ ብሔራዊ ሆስፒታል ነርስ እና የማዳራካ ኤክስፕረስ ተሳፋሪ የሆነችው ሜሪ ኒሃ በዶ/ር ኢንዳኒኒ ሉሴሶ በመታገዝ የማዋለድ አገልግሎቱን ሰጥተዋል፡፡እናትም ሆነ ሕፃኑ ደህና መሆናቸዉን የኬንያ ምድር ባቡር ገልጿል።በርካቶች ህፃኑ ነፃ ቲኬቶችን የማግኘት መብት ሊኖረው ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ሌሎች ደግሞ አዲስ የተወለደው ህጻን ማዳራካ ተብሎ እንዲጠራ ሐሳብ ያቀረቡ ሲሆን በስዋሂሊ ቃል “ኃይል” ማለት ነው፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *