
ሁለቱ የዓለማችን ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ታዋቂ ኩባንያ ባለቤቶችና ቢሊየነሮች ኢሎን ማስክ እና ማርክ ዙከርበርግ በቦክስ ግጥሚያ እርስ በርስ ለመፋለም ተስማምተዋል።ማስክ ከዙከርበርግ ጋር “ለመፋለም ተዘጋጅቻለዉ” በማለት በማህበራዊ ሚዲያው ትዊተር ላይ መልእክት አስፍሯል።
የፌስቡክ እና የኢንስታግራም የወላጅ ኩባንያ ሜታ ኃላፊ ዙከርበርግ በመቀጠል ማስክ የፃፈዉንን የትዊተር ስክሪን ሾት በማድረግ የምንፋለምበትን “ቦታ ላክልኝ” ከሚል መግለጫ ጋር አጋርቷል፡፡ማስክ በማስከተል ለዙከርበርግ በሰጡት ምላሽ “ቬጋስ ኦክታጎን” ላይ ግጥሚያዉ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
ኦክታጎን ለUFC ፕሮሬሽናል ቡጢኞች ውድድር የሚያገለግል ስፍራ ሲሆን በላስ ቬጋስ፣ ኔቫዳ ዉስጥ ይገባል፡፡በዚህ ወር መጨረሻ ላይ 52ኛ ዓመቱን የሚያከብረዉ ማስክ በትዊተር ገፃቸውም ባጋሩት ሀሳብ ዙከርበርግ ያቀረበው ፈተና ሙሉ በሙሉ ከባድ ላይሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።
አክሎም “ልጆቼን ከማንሳት እና በአየር ላይ ከመልቀቅ በስተቀር በጭራሽ ልምምድ አልሰራም ማለት ይቻላል ”ብሏል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የ39 አመቱ ሚስተር ዙከርበርግ በድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ስልጠና ሲወስድ የቆየ ሲሆን በቅርቡ የጂዩ-ጂትሱ ውድድሮችን አሸንፏል።የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ውድድሩን ማን እንደሚያሸንፍ ሲከራከሩ ቆይተዋል፣ ሌሎች ደግሞ የትግል ዉድድሩን የሚያስተዋውቁ አስቂኝ ፖስተሮችን እያጋሩ ይገኛሉ፡፡ለምሳሌ፣ የቢዝነስ አማካሪው ሰዪ ቴይለር በትዊተር ገፃቸው “ተዋጊህን ምረጥ” ባለዉ ጹሁፍ ላይ የሁለቱን የቴክኖሎጂ አለቆች ምስሎች አጋርቷል፡፡
በስምኦን ደረጄ