
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እና የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሞዲ አመራር የተፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በተመለከተ በዋይት ሀውስ ጥያቄዎች ቀርበዉላቸዋል፡፡ መሪዎቹ በሚቀጥሉት ዓመታት በሁለቱ ሀገራት ስለሚኖረዉ ዘላቂ አጋርነት መክረዋል፡፡የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በዩናይትድ ስቴትስ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ሐሙስ ዕለት አጭር መግለጫ ሰጥተዋል፡፡በምሽቱ በኋይት ሀውስ በከፍተኛ ደረጃ የመንግስት እራት ግብዣ ተደርጎላቸዋል፡፡
የባይደን አስተዳደር ለቀረበበት ትችት ምላሽ እንዲሰጡ ባይደን ሲጠየቁ በሞዲ አስተዳደር በጂኦፖለቲካል ስም የተፈፀመውን የመብት ጥሰት በመመልከት “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና እኔ ስለ ዲሞክራሲያዊ እሴቶች ጥሩ ውይይት አድርገናል” ብለዋል።የሞዲ መንግስት ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እየገደበ፣ አናሳዎችን በመጉዳት እና ተቺዎችን በማፈን ሰፊ ክስ ከመብት ተሟጋች ድርጅቶች የቀረበባቸዉ ሞዲ ትችቱ “አስገረመኝ” ሲሉ ጠንከር ባለ ቃና ተናግረዋል።
እሮብ እለት ሞዲ የዮጋ መርሃ ግብርን ኒውዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት አስተናግደዋል፡፡በዋሽንግተን ውስጥ ሁለቱም መሪዎች በቀጣዮቹ ዓመታት ጠንካራ አጋርነት አስፈላጊነትን በማወደስ ፣ በ ኢንዶ ፓሲፊክ መረጋጋት ዙሪያ እና በቻይና እያደገ ስላለዉ ተጽዕኖ መክረዋል፡፡
በስምኦን ደረጄ