መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 20፤2015-በኩሪፍቱ ሀይቅ ለመዋኘት የገባው የሩሲያ ዜጋ ህይወቱ አለፈ

በቢሾፍቱ ኩርፊቱ ሀይቅ በመዝናናት ላይ ከነበሩት የዉጭ ሀገር ዜጎች መካከል አንድ የሩሲያ ዜግነት ያለዉ የ 55 ዓመት ህይወቱ ማለፉን እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተያገሩት ግለሰቡን ለሞት ያበቃዉ በኩሪፍቱ ሀይቅ 1መቶ 50 ሜትር ድረስ ርቀት ሀይቁን ዘልቆ በመዋኘት ላይ ሳለ መመለስ ሳይችል ቀርቶ ነው ብለዋል።

ዋና ለመዋኘት የገባዉ እሁድ ሰኔ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ሲሆን የኮሚሽን መ/ቤቱ ጠላቂ ዋናተኞች ትላንት ሰኔ 19 እለት ከሁለት ሰዓት ፍለጋ በኋላ አስከሬኑን አግኝተዉታል ሲሉ ጨምረዉ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በትግስት ላቀዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *