
በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት ሰኔ 23 ከቀኑ 6 ገደማ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታዉ ሰሜን ሆቴል ፊት ፊት በሲኖትራክ ተሽከርካሪ በደረሰ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3_ኢት A04091 የሆነ ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ መንገድ በመሻገር ላይ ያለ ዕድሜዉ 50 ዓመት የተገመተ ሰዉ ገጭቶ ህይወቱ አልፏል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በተሽከርካሪዉ ተገጭተው ህይወቱ ያለፈዉን ግለሰብ አስከሬን ከተሽከርካሪዉ ስር በማሸነሪ ታግዘዉ አዉጥተዉታል።
ትላንት ምሽት 3:43 ሰዓት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ጣፎ 2 ኛ በር አካባቢ መንገድ ሲጠቀም የነበረ የ44 ዓመት እግረኛ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-53457 በሆነ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ተገጭቶ ህይወቱ ማለፉን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል ።
በትግስት ላቀው