መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 26፤2015-እስራኤል በዌስት ባንክ ጄኒን ከተማ ላይ በወሰደችው ጥቃት ሁለት ፍልስጤማውያን ተገደሉ

የእስራኤል ጦር በዌስት ባንክ ከተማ ጄኒን በሚሳኤሎችና ሄሊኮፕተሮችን በመጠቀም በፈፀመው የአየር ጥቃት ቢያንስ ሁለት ፍልስጤማውያንን ሲገደሉ ሌሎች 10 ሰዎች መቁሰላቸውን የመንግስት ባለስልጣናት እና እማኞች ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ እንዳሉት ቢያንስ አራት የእስራኤል የአየር ጥቃቶች በዛሬው እለት በጄኒን ከተማ ውስጥ የሚገኙ ሕንፃዎች መምታታቸውን ገልፀዋል።

ጥቃቱን ተከትሎ የከተማዋ ከፊል ክፍል በጭስ ተሸፍኖ የነበረ ሲሆን የእስራኤል የታጠቁ ተሽከርካሪዎች ወደ ከተማዋ የስደተኞች ካምፕ ሲንቀሳቀሱ ማየታቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።በጄኒን የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ዳይሬክተር የሆኑት ማህሙድ አል ሳዲ የአየር ላይ የቦምብ ጥቃት እና በመሬት ላይ ደግሞ ወረራ እየተካሄደ ነው ሲሉ ለ AFP የዜና አገልግሎት ተናግረዋል።

“በርካታ ቤቶች እና ስፍራ በቦምብ ተወርውረዋል ጭሱ ከየቦታው እየጨመረ ነው” ሲል የፍልስጤም የጤና  ሚኒስቴር ያስታወቀ ሲሆን ጉዳት ከደረሰባቻው 10 ሰዎች መካከል አንዱ በከባድ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል ተብሏል።በዛሬው እለት የተፈፀመው ወረራ በዌስት ባንክ እ.ኤ.አ ከ 2006 በኃላ እስራኤል የመጀመሪያውን ሰው አልባ ጥቃት ፣ በጄኒን እና በሰሜናዊ የፍልስጤም ግዛቶች ላይ የወሰደችው ተደርጎ ተመዝግቧል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *