
ከጋዛ ሰርጥ ሮኬቶች ወደ እስራኤል መተኮሳቸውን ተከትሎ ዛሬ ረቡዕ ማለዳ እስራኤል የአየር ላይ ጥቃት እርንጃ መውሰዷን ከጋዛ ለአልጀዚራ የሚዘግበው ኢሳም አድዋን ተናግሯል። “በተለይ በጋዛ ሰርጥ ሰሜናዊ በኩል በቤቴ ላሂያ ከተማ እና በደቡብ በኩል በጋዛ ከተማ የተለያዩ የአየር ጥቃቶች ሲፈፀሙ አይተናል” ሲል አድዋን ተናግሯል።
የፍልስጥኤም የጤና ሚኒስቴር በጥቃቱ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የገለፀው መረጃ የለም።የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሐኪሞች ቡድን እንዳስታወቀው የእስራኤል ወታደራዊ ጥቃት በጄኒን ላይ ባደረሰው ውድመት ሶስት ሆስፒታሎች ጥቃት ደርሶባቸዋል ብሏል። “የተቋማቱን አቅማቸውን በእጅጉ ይጎዳል” ሲል አክሏል።
የእስራኤል ጦር በጄኒን ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ አምቡላንስ የቆሰሉትን ሰዎች እንዳያስወጣ መከልከሉ እና “በተጨማሪ የእስራኤል ወታደሮች አስለቃሽ ጭስ እና በቀጥታ ጥይቶችን በመተኮስ በጄኒን የመንግስት ሆስፒታል ውስጥ ገብተዋል” ሲል የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኑ በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል።
ማሌዥያ በዌስት ባንክ ጄኒን የደረሰውን የአየር ጥቃቶች አውግዛለች። እስራኤል “ደም መፋሰሱን እንድታቆም” እና የጄኒን ህዝብ የሰብአዊ እና የጤና አጠባበቅ አገልግሎቶችን ያለ ምንም እንቅፋት እንድትፈቅድ ጠይቃለች ።
በስምኦን ደረጄ