መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 28፤2015-የኬኒያ ሴቶች የሚወልዷቸው ልጆች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ተነገረ

በኬንያ ባለፉት አስር ዓመታት ሴቶች ለመውለድ የሚፋልጉት የልጆች ብዛት እየቀነሰ መሆኑን አንድ አዲስ መረጃ አመላክቷል። ነገር ግን መንግስት በኬንያ የስነ-ህዝብ ጤና ዳሰሳ ግኝቶች ላይ በመመስረት የሀገሪቱ ህዝብ አሁንም ማደጉን ስለሚቀጥል ኬንያውያን መጨነቅ የለባቸውም ብሏል።

በኬኒያ የወሊድ መጠን በ2014 በአማካይ 3.9 የነበረ ሲሆን በ 2022 ዓመት ወደ 3.4 ዝቅ ብሏል ። ይህ ማለት በአሁኑ ጊዜ በኬንያ ከ15 እስከ 49 ዓመት የሆነች አንዲት ሴት በፊት ሊኖራት ከሚችለው ከአራት ልጆች ይልቅ ሶስት ልጆችን የመውለድ ዕድሏ ከፍተኛ ነው። እ.ኤ.አ. በ 1989 በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ  ያሉ ሴቶች እስከ ሰባት ልጆች ነበሯቸው።

የጤና ባለሙያዎች የቤተሰብ ምጣኔ ዘዴዎች ተደራሽነት መጨመር አጠቃላይ የወሊድ መጠን እንዲቀንስ አድርጓል ይላሉ። የትምህርት ደረጃ ለማሻሻል በሴቶች የሚደረጉ ጥረቶች ልጅ የመውለድ ሂደትን እያዘገየ ይገኛል ። እንደ ሪፖርቱ በሀገሪቱ እየጨመረ የመጣው የኑሮ ውድነት የህጻናትን አስተዳደግ ምርጫም ጎድቷል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *