መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 30፤2015-በጎፋ ዞን በ29 የፖሊስ አመራር እና አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተነገረ

የጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ በዞኑ ስር በሚገኙ በሁሉም ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደር የፖሊስ መዋቅሮች ሲያከናውን የነበረውን ዞናዊ መድረክ አጠናቋል ።በግምገማ መድረኩ የተወሰዱ እርምጃዎች የተነሱ ሲሆን በዚህም መሰረት 70 የፖሊስ አባላት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ፣ 20 የፖሊስ አባላት ደግሞ ከኃላፊነት እንዲነሱ ውሳኔ የተላለፈ መሆኑ ተጠቅሷል።

በተጨማሪ ስድስት የፖሊስ አባላት ላይ በስነምግባር እንዲጠየቁ እና ሶስት አባላት ደግሞ ከሥራ ታግደው በህግ መጠየቅ እንዳለባቸዉ ተገልጿል ። በአጠቃላይ 29 የፖሊስ አመራር እና አባላት ላይ እርምጃ ተወስዶ 70 የፖሊስ አባላት ላይ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ መጠናቀቁን የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አ/ቶ ካሳሁን አባይነህ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ በየደረጃው በፖሊስ አመራር እና አባላት ዘንድ የሚታዩ የአመለካከት ፣ የአሰራር ፣ የአመራር እና የሥነ-ምግባር ግድፈቶችን በማረም ለህብረተሰቡ ወቅቱን የሚመጥን አገልግሎት ማበርከት የሚያስችል የግምገማ ሰነድ በማዘጋጀት ወደ ግምገማ ሂደት እንደተገባ አ/ቶ ካሣሁን አክለዋል ።

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *