መደበኛ ያልሆነ

ሀምሌ 3፤2015-ላምበረት አካባቢ በሚገኝ ሆቴል በደረሰ የእሳት አደጋ በመኝታ ክፍል ውስጥ የነበሩ አንዲት ሴትና ወንድ ህይወታቸው አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ ትላንትና ምሽት 3:30 ላምበረት አካባቢ በሚገኝ ሆቴል በደረሰ የእሳት አደጋ ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው አልፏል። በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ ወጣቶቹ ወደ ክፍለሀገር ለመሄድ አልጋ ይዘው የነበሩ መሆናቸውን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

አደጋው በየካ ክፍለከተማ ወረዳ 9 ላምበረት መናህሪያ  አካባቢ በሚገኝ ሆቴል የደረሰ ሲሆን እድሜያቸው 26 እና 24 ዓመት የሆኑ ወንድ እና ሴት ወጣቶች በጭስ ታፍነው ህይወታቸውን ማለፉን  የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በአደጋው ሆቴል ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል።የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር  አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎችና 40  የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተዋል። 30 ሺ ሊትር ውሃ በመጠቀም የእሳት አደጋዉ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርሰ መቆጣጠር ተችሏል።

የእሳት አደጋዉን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር 1:ሰዓት ከ 37 ደቂቃ ፈጅቷል።ሆቴሉን የአደጋ መመሪዎችን እና መስፈርትን እንደማያሟላ አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *