መደበኛ ያልሆነ

ሀምሌ 3፤2015-ቅዱስ ሲኖዶስ ለትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ እና መልሶ ግንባታ የ20 ሚልየን ብር ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጦርነቱ ወቅት ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰበት የትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ እና ለመልሶ ግንባታ የሚውል የ 20 ሚልየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የቅዱስ ሲኖዶሱን የገንዘብ ድጋፍ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በዛሬው ዕለት ለክልሉ ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ማስረከባቸውን ብስራት ራዲዮ ከቤተክርስቲያኒቱ የመገናኛ ብዙኀኖች ካገኘዉ መረጃ ተመልክቷል።

በዛሬው ዕለት ቅዱስነታቸውን ጨምሮ የቅዱስ ሲኖዶሱ የሰላም ልዑክ ይህንን ድጋፍ ለማስረከብ እና በትግራይ ክልል ከሚገኙ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ለመወያየት ወደ መቐለ ማቅናቱ ይታወቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *