መደበኛ ያልሆነ

ሀምሌ 3፤2015-ከሴኔጋል 200 ስደተኞችን ያሳፈረች ጀልባ በካናሪ ደሴቶች ላይ መጥፋቷ ተሰማ

የስፔን የነፍስ አድን ሰራተኞች ከሳምንት በላይ የጠፋውንና ከ200 ያላነሱ አፍሪካውያን ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ለማግኘት ከካናሪ ደሴቶች ዳርቻ ላይ ፍለጋ እያደረጉ ይገኛል። የነፍስ አድን ቡድኑ ዎኪንግ ቦርደርስ እንዳስታወቀው የዓሣ ማጥመጃ ጀልባው ከቴኔሪፍ 1,700 ኪ.ሜ ርቀት ከደቡብ ሴኔጋል የባሕር ዳርቻ ከምትገኘው ካፎውንታይን የባህር ዳርቻ ከተማ መነሳቷን ገልጿል።

የስፔኑ ኢፌ የዜና ወኪል እንደዘገበው ቡድኑ በርካታ ህጻናት በጀልባው ውስጥ መሆናቸውን አረጋግጧል ብሏል። በርካታ ሰዎችን ያሳፈሩ ሁለት ተመሳሳይ ጀልባዎችም ጠፍተዋል ተብሏል። ወደ 200 የሚጠጉ ሰዎችን የጫነችው ጀልባ በሰኔ መጨረሻ ከካፎውንቲን ተነስታ ወደ ካናሪ ደሴቶች አምርታለች። የስፔን የባህር አድን አገልግሎት አንድ አውሮፕላን በማሰማራት ፍለጋውን ቀጥሏል።

ስለ ሌሎቹ ሁለት  የጠፉ ጀልባዎች ሮይተርስ የዜና ወኪል በሰራው ዘገባ አንደኛዋ 65 የሚጠጉ ሰዎች ማሳፈሯንና  ሌላኛው ደግሞ እስከ 60 የሚደርሱ ሰዎችም አሳፍራ ነበር ብሏል። ይህም በሶስቱ ጀልባዎች ላይ የጠፉትን ሰዎች ቁጥር ከ300 በላይ ያደርሰዋል።ይህው ዜና በሜዲትራኒያንያን ባህር ዳርቻ አስከፊ የመርከብ መሰበር ከተሰማ ከሳምንታት በኋላ ያጋጠመ ሲሆን በግሪክ የባህር ዳርቻ አደጋ ማጋጠሙ ይታወሳል። በአደጋው ቢያንስ 78 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ የተረጋገጠ ቢሆንም እስካሁን 500 የሚደርሱ ሰዎች ደብዛቸው መጥፋቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *