መደበኛ ያልሆነ

ሀምሌ 3፤2015-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ የማይቻል መሆኑን አስታወቀ ❗️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚቀጥሉት 6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን አስታወቀ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የኑሮ ውድነቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ የቤት ኪራይ ጭማሪ እንዳይደረግ በተለያዩ ተከታታይ ጊዜያት ውሳኔ ማሳለፉን አስተዳደሩ አስታውሷል፡፡

በቀጣይም በግል ከሚደረግ ስምምነት ውጪ ማንኛውም አከራይ ለሚቀጥሉት 6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን መገለጹን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *