መደበኛ ያልሆነ

ሀምሌ 4፤2015-በጂንካ ከተማ በስለት ተወግቶ ህይወቱ ካለፈው ወጣት ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

በጂንካ ከተማ 01 ቀበሌ በሰላም ቀጠና ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ገደማ ከተፈፀመው የወጣት ማቲያስ ጥሩነህ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተነግሯል ።

የከተማ አስተዳደሩ ድርጊቱን የሚያወግ የሀዘን መግለጫ ማውጣቱና ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የጂንካ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ሀላፊ አ/ቶ የሱፍ አህመድ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።

ከወጣቱ ግድያ ጋር በተያያዘ አንዳንድ አካላት ማህበረሰቡን የሚከፋፍል እና የሚለያይ ሀሳብ ከመስጠት መቆጠብ አለባቸው ብለዋል ። በመሆኑም ህብረተሰቡ ለፖሊስ አስፈላጊውን መረጃ በመስጠት የድርጊቱ ፈፃሚዎች በህግ እንዲጠየቁ እንዲተባበር አሳስበዋል ።

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *