መደበኛ ያልሆነ

ሀምሌ 6፤2015-ዛንዚባር ሹርባ የሚሰሩ ወንዶችን በስድስት ወር እስራት እንደምትቀጣ አስታወቀች

የዛንዚባር ባለስልጣናት ወንዶች ፀጉራቸውን ሹሩባ ተሰርተው ከተገኙ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ገልፀዋል። የወንዶች ፀጉራቸውን ሹሩባ መሰራት ህግን የሚፃረር እና የአካባቢውን ወጎች የጣሰ ብሎም የሰዎችን ስነ ምግባር አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን አስታውቋል።

የዛንዚባር የባህል ሥራ አስፈፃሚ ኦማር አደም “ለወደፊት ትውልዶቻችን አደገኛ ሆኖ አግኝተነዋል” ብለዋል። የወንድ ልጅ ፀጉር ሹሩባ መሰራት በዛንዚባር ውስጥ እንደ ነውር ይታያል በማለት ከዛንዚባር ባህል ውጭ የተወሰደ ነው ሲሉ አክለዋል።

ማንም ሰው ወደ ዛንዚባር የገባ ወይም የሚኖር ጸጉሩን ሹሩባ የተሰራ እንደሆነ ከ400 የአሜሪካን ዶላር በላይ ወይም የስድስት ወር እስራት ይቀጣል። ወይም ሁለቱም ቅጣቶች ሊተገበሩበት ይችላል።

ምንም እንኳን ዛንዚባር ከዋና የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል ብትሆንም፣ ባለሥልጣናቱ ህጉ የውጪ ሀገር ጎብኚዎችን እንደሚያካትት ተናግረዋል።ዛንዚባር በታንዛኒያ ውስጥ የምትገኝ ራስ ገዝ ግዛት ነች።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *