መደበኛ ያልሆነ

ሀምሌ 6፤2015-የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በሀረር ከተማ የተገነባው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ ተመረቀ

የዳቦና ዱቄት ፋብሪካው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሚስራ አብደላ  መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

በመድረኩ ላይም ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንዳሉት በሀረር ከተማ የተገነባው የዳቦና የዱቄት ፋብሪካ ሰባተኛ ፋብሪካ ነው።

ፋብሪካው በቀን 420 ኩንታል ዱቄት እና 300 ሺህ ዳቦ እንደሚያመርት ጠቁመው ፋብሪካው ከ150 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል ፈጥሯል ማለታቸዉን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

ፋብሪካው ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲሰራና ለህዝቡ የዳቦ ምርት ተደራሽ እንዲሆን ከማድረግ አንፃር የሚመለከታቸው አካላት በትኩረት እንዲሰራ ጠይቀዋል።

የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሚስራ አብደላ የቀዳማዊ እመቤት ጽ/ቤት በከተማው ያስገነባው የዳቦ እና የዱቄት  ፋብሪካ በተለይም በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደረው የማህበረሰብ ክፍልን በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *