መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 12፤2015-ሆንግ ኮንግ አጫሾችን አፍጥጦ በመመልከት ሲጋራ የሚጨስባቸውን ቦታዎች ለመቀነስ እየሞከረች ትገኛለች

የቻይና አካል ሆና በራስ ገዝ መስተዳድር የምትተዳደረው ሆንግ ኮንግ ከሲጋራ የፀዱ አካባቢዎችን ለመፍጠር  የተለያዩ ጥብቅ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች።

ቁጥጥሩም ፍሬ ያፈራ ይመስላል። በ1980ዎቹ ከህዝቧ 23 በመቶ የሚሆነውን ሲጋራ አጫሽ ወደ 10 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏታል።

በሆንግ ኮንግ ሰው በተሰበሰበባቸው ቦታዎች ሲጋራ ማጨስ ፈፅሞ የተከለከለ ቢሆንም አልፎ አልፎ ግን ህጉ ሳይፈፀም የሚቀርበት ጊዜ አለ።

ለዚህ ነው የሆንግ ኮንግ ጤና ሚኒስትር  ፕሮፌሰር ሎ ቹንግ ማው አጫሾች ላይ ማፍጠጥን እንደ መፍትሔ የወሰዱት።

ፕሮፌሰሩ <<በሬስቶራንትም ሆነ ሰው በተሰበሰበበት ስፍራ ሲጋራ ለመለኮስ ከኪሳቸው የሚያወጡትን አፍጥጡባቸው። አስተያየታችሁ ኮስተር ያለ ይሁን። ያኔ አይሞክሩትም>> ይላሉ።

ሚኒስትሩ <<እስኪ የአውቶብስ ሰልፍን ተመልከቱ። ተሰለፉ የሚል ህግ የለም። ግን ሰዎች በራሳቸው ልማድ ይሰለፋሉ። ይሄንን ልምምድ በሲጋራ አለማጨስ ላይ ልናመጣው ይገባል። ይህም ከሲጋራ የፀዱ ከተሞችን ለመፍጠር ያስችላል>> ሲሉ መናገራቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *