መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 19፤2015-በህንድ ፍቅረኛዋን በድብቅ ለማግኘት ስትል የመንደሩን የኤሌክትሪክ ኃይል ስታጠፋ የነበረችው ወጣት ተያዘች

በህንድ ቢሃር ግዛት የምትኖር አንዲት ወጣት ከፍቅረኛዋ ጋር ማንም ሳያያቸው ለመገናኘት በሚል የመንደሩን የኤሌክትሪክ ኃይል ስታጠፋ መቆየቷ ተደርሶባተል። ፍቅረኛዋ ከሌላ ሰፈር የሚመጣ ሲሆን የሰፈሯ ልጆች ይህንን ካዩ ፀብ ይቀሰቀሳል በሚልና በሁለቱ መንደሮች መካከል ዘለግ ላሉ ዓመታት ግጭት  ስለነበር ይህንኑ መንገድ መርጣለች።

በቢሃር ግዛት ምዕራብ ሻምፓራን አውራጃ ውስጥ በምትገኝ የቤቲያህ መንደር በየምሽቱ በሚባል ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል  መቆራረጥ ከአንድ ሳምንት በላይ አስቆጥሯል። ድቅድቅ ጨለማው ለሌቦች አመቺ ሆኖ ስርቆት እንዲበራከት ምክንያት ሆኗል።

ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያስተካክል ጥሪ ባቀርቡም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ኃይል ተወካዮቹ ግን ምንም አይነት የመሠረተ ልማት ችግር እንደሌለ ተናግረዋል። አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች በመንደሩ ውስጥ ነቅተው ሲመለከቱ ታዲያ ጨለማውን ተገን አድርገው ተሸፍነው የሚገናኙ ጥንዶችን ያስተውላሉ።የአካባቢው ተወላጅ የሆነችው ፕሪቲ ኩማሪ ከተቀናቃኝ መንደር ከሚኖረው ፍቅረኛዋ ራጅ ኩማር ጋር በፍቅር ወድቃ ነበር እና ግንኙነቱን ሚስጥራዊ ለማድረግ በየጊዜው የመንደሩን የኤሌክትሪክ መስመር ስትቆርጥ እንደቆየች ተደርሶባታል።

ፕሪቲ መብራት ታጠፋ በነበረበት ቀናቶች በመንደሩ ውስጥ በርካታ ስርቆቶች ይፈጸሙ ነበር። በህንድ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተለቀቀ ምስል ጥንዶቹ ሲያዙና ፕሪቲ ፍቅረኛዋን ከመንደሩ ወጣቶች ድብደባ  ለመከላከል ስትሞክር ያሳያል። ራጅኩማር በፍቅረኛው መንደር የደረሰበትን ድብደባ ከራሱ ሰፈር ጓደኞች ጋር በመምጣት አጥቂዎቹን ተበቅሏል።ይህው ፀቡ በሁለቱ መንደሮች ከዚህ በላይ እንዳይጋጋል ጥንዶቹ ጋብቻ እንዲመሰርቱ በአካባቢው ነዋሪዎችን ይሁንታን አግኝተዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *