መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 21፤2015-በአዲስ አበባ በ2015 ዓመት ከፍተኛ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ የደረሰው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ መሆኑ ተነገረ

በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት 495 ድንገተኛ አደጋዎች መድረሱን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል፡፡ በዚሁ ጊዜ ውስጥ ከደረሰ አደጋዎች መካከል 326ቱ የእሳት ቃጠሎ ሲሆን 169ኙ አደጋዎች ደግሞ ከእሳት ውጪ የሆኑ ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ስለ መሆናቸው የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮና ቲቪ ተናግረዋል።

ከደረሰቱ አደጋዎች ውስጥ 76 በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ በመሆኑ ክፍለከተማው በአደጋ ብዛት የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በመቀጠል አዲስ ከተማ 52 የእሳት እና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች በመድረሳቸው ሁለተኛ እንዲሁም ቦሌ ክፍለከተማ 48 የእሳት እና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ደርሰው በሶስተኛ ደረጃ ተቀምጣል፡፡

በዓመቱ ዝቅተኛ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ የደረሰባቸው ክፍለከተሞች ልደታ፣  አራዳ እና ጉለሌ መሆናቸውን ኮሚሽኑ አስታውቃል፡፡ከተከሰቱት አደጋዎች 425 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክልል ውሰጥ የተከሰቱ ሲሆን በአማራ ክልል 1 በኦሮሚያ ልዩ ዞን የተከሰተ አደጋ 69 መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በዓመቱ በደረሱት ድንገተኛ አደጋዎች 110 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ 165 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሷል።በተጨማሪም 20 ሰዎችን ከተለያዩ አደጋዎች በህይወት ማትረፍ ተችሏል።በ 2015 ዓመት የደረሰው የእሳት አደጋ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ36 ያህል የቀነሰ ቢሆንም በድንገተኛ አደጋ ረገድ ግን በ20 መጨመሩ ተገልጿል።

ኮሚሽኑ በስራ ላይ ያጋጠማቸው የተለያ ችግሮች እንደነበር ያስታወቀ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በስራ ክፍሉ ውስጥ ያለ ስልክ መብራት ሲጠፋ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑ ተነስቷል። በተጨማሪም በመረጃ ቅብብል ወቅት የሬድዮ መቆራረጥ፣ያለምንም ፈቃድ ከስራ ገበታ ላይ መቅረት፣የመረጃ ሰራተኞች የአደጋ መረጃ በተደራጀ መንገድ ተቀብሎ የማስተላለፍ እና የግብዓት ችግር መሆናቸውን ተመላክቷል፡፡

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *