መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 21፤2015-ከዘረፏት በኋላ ከባጃጅ ውስጥ ወርውረው ለሞት የዳረጓት ተጠርጣሪዎች በቁቁጥር ስር ዋሉ።

በሐረር ከተማ መጋቢት 13/2015 አመሻሽ 1:30 አካባቢ በተለምዶ ሞቢል ተብሎ በሚጠራው ሰፈር በሶስት እግር ተሽከርካሪ(ባጃጅ) የዝርፊያ ተግባር በሚፈፅሙ ሌቦች የተገፈተረች ወጣት ህይወቷ ማለፉ መገለጹ ይታወሳል።

ዛሬ ላይ የሐረሪ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው ሟች የኔ ወረቅ አበበን ከምትማርበት ሐረር መምህራን ኮሌጅ ወደ ቤት ስትመለስ ከተሳፈረችበት የሦስት እግር ተሽከርካሪ ውስጥ ወርውረው ህይወቷ እንዲያልፍ ያደረጉ ግለሰቦች በሙሉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

የሀረሪ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ጃቢር አሊ እንደገለጹት 1ኛ ሮቤል አህመድ ዋና ንጥቅያ የፈፀመ 2ኛ ዳግም ቴውድሮስ አለማየው የባጃጁ ሹፌር የነበረ 3ኛ በቅፅል ስሙ ኪያ ተብሎ የሚጠራ በጋራ በመሆን ሟችን ባጃጅ ውስጥ ካስገቧት በኋላ ቦርሳዋን ታግለው በመጠቅ ከቲቪኤስ ውስጥ ወርውረዋት ከመንገዱ በተቃራኒ በኩል ይጓዝ የነበረ ቅጥቅጥ ሀይሱዙ አውቶብስ ተሽከርካሪ ተገጭታ እንድትሞት ማድረጋቸውን ነው የገለጹት።

ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን ከፈፀሙ በኋላ በሱማሌ ክልል ተሸሽገው እንዳሉ የሐረሪ ፖሊስ ባደረገው ክትትል እና ጥልቅ ምርመራ ሁሉም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው ተጠናቆ ለአቃቢ ህግ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በወቅቱ ሟችን የገጨ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3 – 351639 ኦሮ ቅጥቅጥ ሀይሱዙ አውቶብስ መኪና ምርመራው ተጠናቆ ለአቃቢ ህግ መሠጠቱንም የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ጃቢር አሊዪ መግለጻቸውን የሐረሪ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *