የ ‘UAE’(የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ) ስኮላርሽፕ አግኝተዉ የዩኒቨርሲቲ ምደባ ያላገኙ ቀሪ 73 ተማሪዎች ምደባችሁ የታወቀ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁን ብስራት ራዲዮ እና ቴቪ ሰምቷል።
በዚህም መሰረት ተማሪዎች የተመደቡባቸዉን ዩኒቨርስቲዎች እና ከየዩነቨርሰቲዉ የምታገኙትን ሰዉ (Contact person) የኢሜል አድራሻ የተቀመጠ ስለሆነ በአድራሻዉ እየተጻጻፋችሁ የምትጠየቁትን እንድታሟሉ ሲል ገልጿል፡፡
ተማሪዎች የተመደቡባቸዉን ዩኒቨርሲቲዎች ዝርዝር ለመመልከትም http://rb.gy/pzdd4 እንዲጠቀሙ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።