መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 26፤2015-የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹን መቀበል ጀመረ

የመቐለ ዩኒቨርስቲ በ2013 ዓ.ም ተመራቂ ለነበሩ የመጀመርያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች፣
የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ፣ የተከታታይ ትምህርትና የማታ ተማሪዎች እንዲሁም የህክምና ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ሐምሌ 26 እና 27/2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው በአካል በመገኘት ምዝገባ እንዲያደርጉ ባሳሰበዉ መሰረት በዛሬዉ እለት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲዉ መግባት መጀመራቸውን ብስራት ራዲዮ እና ቴቪ ከክልሉ መገናኛ ብዙኃን ተመልክቷል። ተማሪዎቹ ከሶስት አመታት በኋላ ነዉ ወደ ዩኒቨርስቲው የተመለሱት።

ዩኒቨርስቲው በተመሳሳይ ተመራቂ ላልሆኑ የመጀመርያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 04 እና 05/2016 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ሬጂስትራር ጽ/ቤት ማሳወቁ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *