መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 28፤2015-የሞሮኮ ንጉስን በፌስቡክ ገፁ ላይ የተቸው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

የሞሮኮን ንጉስ በማህበራዊ ሚዲያ በመተቸት የተከሰሰው ግለሰብ በአምስት ዓመት እስራት መቀጣቱን ጠበቃው ደንበኛቸውን በማስመልከት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ሰይድ ቡክዩድ የተባለው ግለሰብ እ.ኤ.አ በ2020 ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር የነበራትን የሻከረ ግንኙነት በማደስ መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጀመሯን በመንቀፍ በፌስቡክ ላይ በለጠፋው አስተያየት “ንጉሣዊውን አገዛዝ በማዳከም” በሚል ተከሷል።

በወቅቱ ይህንን መልዕከት በፌስቡክ ገፁ ላይ ሲያሰፍር ሰይድ ቡክዩፍ በኳታር ይኖሩ ነበር። በሞሮኮ ሕገ መንግሥት መሰረት ንጉሥ መሐመድ ስድስተኛን   ሥልጣናቸውን የሚጠራጠርና የሚያዳክም የሚመስሉ አስተያየቶች ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ይደነግጋል።

የቡክዩድ ጠበቃ ኤል ሀሰን ኢሶዩኒ ቅጣቱን “ጨካኝ እና ለመረዳት የማይቻል” ሲሉ በደንበኛቸው ጉዳይ ይግባኝ እንደሚሉ ገልፀዋል።እስራኤል ሞሮና በታላቁ የአብርሃም ስምምነት በሚባለውና በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተመራው የእርቅ ስምምነት ያላቸውን የሻከረ ግንኙነት ማዳሳቸው ይታወሳል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *