መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 3፤2015-በመዲናዋ በሞተር ብስክሌቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተራዘመ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ላይ ጥሎት የነበረውን እግድ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን አስታወቀ፡፡

ቢሮው ሐምሌ 27/2015 ባወጣው መመሪያ እስከ ነሐሴ 3/2015 ዓ.ም የሞተር ብስክሌቶችን በከተማዋ ማሽከርከር እንደማይቻል መግለጹን አስታውሶ እገዳው ዛሬ ማብቂያ ጊዜ መሆኑን ተከትሎ ነው መመሪያውን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን የገለጸው፡፡፡

ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት ሲሆን የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እግዱ እሰኪነሳ በትዕግስት እንዲጠብቁ ማሳሰቡን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *