መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 5፤2015-በአዲስ አበባ ኤርፖርት ከ247 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው ኮኬይን ተያዘ

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 29.2 ኪ.ግ የሚመዝንና 247.2 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ።

መነሻውን ብራዚል ባደረገ አውሮፕላን ተጭኖ አዲስ አበባ ኤርፖርት የደረሰው ይህ እጽ፤ የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሠራተኞች ባደረጉት ጥብቅ ፍተሻ ሊያዝ መቻሉን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል።

ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን መምሪያ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች፣ የፌደራል ፖሊስ አመራሮች አደንዛዥ ዕፁ እንዲያዝ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውም ተገልጿል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *