መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 10፤2015-የቀድሞ የደቡብ አፍሪካን ቀዳማዊት እመቤት ለገደለ ሰው ይቅርታ ተደረገለት

የደቡብ አፍሪካን የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ማሪኬ ደ ክለርን የገደለው ሰው በነሀሴ ወር መጨረሻ ላይ በይቅርታ እንደሚፈታ ተሰምቷል፡፡

ወንጀሉን ሲፈጽም ይህዉ ሰዉ የ21 ዓመት ወጣት የነበረ ሲሆን ሉያንዳ ምቦኒስዋ ተብሎ ይጠራል፡፡ በቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት መኖሪያ ቤት ውስጥ የጥበቃ ሰራተኛ ሆኖ ሰርቷል።የ64 ዓመቷ ወይዘሮ ደ ክለርክ በታኅሣሥ 2001 በኬፕ ታውን በሚገኘዉ መኖሪያ ቤቷ ውስጥ በስለት ተወግታ ህይወቷ አልፎ ተገኝቷል፡፡

ምቦኒስዋ ይህን ወንጀም ከፈጸመ በኃላ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ የወርቅ ሰዓት እና ገንዘብ ሰርቆ ቢሰወርም ወንጀሉ ከፈጸመ ከሁለት ቀናት በኋላ በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡በግንቦት 2003 በነፍስ ግድያ እና በስርቆት ወንጀል የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ነበር።

ከ20 ዓመታት እስር በኋላ፣ የሚጠበቅበትን አነስተኛውን ጊዜ በእስር ካሳለፈ በኋላ የይቅርታ ምደባ ተደርጎለታል፡፡ወደ ማህበረሰብ እርማት ስርዓት እንዲገባ እና ለቀሪው ህይወቱ የተወሰነ የይቅርታ ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲያከብር ይጠበቅበታል ሲሉ የማረሚያ ቤቶች መምሪያ ቃል አቀባይ ሲንጋባሆ ንክሱማሎ ተናግረዋል።

ማሪኬ ደ ክለር ከ1989 እስከ 1994 ድረስ የደቡብ አፍሪካ ቀዳማዊት እመቤት ነበረች።ባለቤታቸዉ ፍሬድሪክ ቪለም ደ ክለር በአፓርታይድ አገዛዝ የሀገሪቱ የመጨረሻው ፕሬዝዳንት ነበሩ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *